መግቢያ
የራስ አገዝ ጥምረት በራስ አገዝ ቡድን አሰራር መሰረት 3ኛው እና የአሰራሩ መገለጫ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ በስራ ላይ ከሚገኙት ጥምረቶች መካከል በአማራ ክልል ደብረ ብርሃን ከተማ ላይ የሚንቀሳቀሰው ምሳሌ ጥምረት አንዱ ነው፡፡ ይህ ምሳሌ ጥምረት ድረ ገፅ ስለ ጥምረቱ አመሰራረት እና እንቅስቃሴ የሚያስተዋውቅ ነው፡፡ ስለ ምሳሌ ጥምረት የበለጠ ለማወቅ ከታች ያሁትን መረጃዎች እንዲገቡ በክብር እንጋብዛለን፡፡
አብራችሁን ለመስራት በአድራሻችን አግኙን፡፡
+ ስለ ራስ አገዝ ጥምረት ፅንሰ ሀሳብ
በራስ አገዝ አሰራር መሰረት ጥምረት አራት ዋና ዋና የስራ ሚናዎች ይኖሩታል፡፡ እነርሱም፤
1ኛ. ጠንካራ የህዝብ ተቋም መመስረት እና ማስቀጠል
2ኛ. የህብረተሰቡን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ አገልግሎቶችን ማመቻቸት
3ኛ. ለማህበረሰብ ሰላም፤ ደህንነት እና ፍትህ መስራት
4ኛ. በመንግስት ፓሊሲና በህብረተሰቡ አስተሳሰብ ላይ በጎ ተፅዕኖዎችን ማሳደር
+ የምሳሌ ጥምረት አመሰራረት
የቁጥር መረጃዎች ፡- የአባል ቡድኖች ብዛት 100
የሕብረቶች ብዛት 5
ጠቅላላ አባላት ብዛት 2000
አጠቃላይ የቡድኖች ቁጠባ 32,500,000 ብር
አጠቃላይ የቡድኖች ካፒታል 32 ሚሊዩን 576 ሺ 500 ብር
የምሳሌ ጥምረት ራዕይ
- ከድህነት የተቀላቀለች፤ ሰsላምና ፍትህ የሰፈነባት እና እናቶች የተሻለ ሕይወት የሚኖሩባት ኢትዮጵያን ማየት
ተልዕኮ
- የራስ አገዝ ቡድኖች እና ህብረቶች ራዕይ መሳካት እገዛ ማድረግ
- በጅማ ከተማ እናቶች እንዲደራጁ ድጋፍ ማድረግ
- በከተማችን ውስጥ ለሚሰሩ የልማት ስራዎች አስተዋጽኦ ማበርከት፡፡
ግብ
- እስከ 2015 ዓ.ም ድረስ 5000 እናቶችን በራስ አገዝ ቡድን ተደራጅተው ከድህነት ተላቀው ማየት፡፡
+ በጥምረቱ የሚሰሩ ዋና ዋና ስራዎች
1ኛ. በስሩ ላሉ የራስ አገዝ ቡድኖችና ህብረቶች የማጠናከር እ ና ክትትል ድጋፍ መስጠት፤
2ኛ. ማርች 8 አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ክብረ በዓልን በጅማ ከተማ ሴቶችና ህጻናት እንዲሁም ከተለያ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በተለያ ዝግጅቶች ያከብራል፤
3ኛ. በህፃናትና ሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች እንዲቆሙ ከፍትህ አካላት ጋር በመተባበር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በየጊዜው የይሰራል፤
4ኛ. ኤች አይ ቪ፤ የልጆች ጉልበት ብዝበዛ፤ የሴቶችና ህፃናት መብት ጥሰት ወዘተ ዉሪያ የተለያዩ የንቅናቄ እና ዘመጫዎችን ማካሄድ፤
5ኛ. የጅማ ከተማ አስተዳደር በሰጠዉ የመሬት ድጋፍ ለቡድኖች እና ህብረቶች ቢሮዎች እና ቋሚ የገቢ ማስገኛ እንዲኖራችው ማስቻል፤
6ኛ. ከተለያ አካላት ጋር በመተባበር በጅማ ከተማ የአፈር እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ በንቃት መሳተፍ፤
7ኛ. በጅማ ከተማ አስተዳደር ከሄርማታ ቀበሌ ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ፈጽሟል፤
8ኛ. የተለያዩ ስልጠናዎችን ለቡድን እና ህብረት ተወካዮች ያመቻቻል፤
9ኛ. ከአጋር ድርጅቶች ጋር ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ ጊዜው የሚጠይቀውን ስራዎችን ይሰራል፤
10ኛ. የኮሳፕ አመታዊ የጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባዎች ላይ በቋሚነት ይሳተፋል፡፡