መግቢያ
የራስ አገዝ ጥምረት በራስ አገዝ ቡድን አሰራር መሰረት 3ኛው እና የአሰራሩ መገለጫ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ በስራ ላይ ከሚገኙት ጥምረቶች መካከል በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ላይ ጥምረት ለለዉጥ ጥምረት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ይህ የጥምረት ለለዉጥ ጥምረት ድረ ገፅ ስለ ጥምረቱ አመሰራረት እና እንቅስቃሴ የሚያስተዋውቅ ነው፡፡ ስለ ጥምረት ለለዉጥ ጥምረት የበለጠ ለማወቅ ከታች ያሁትን መረጃዎች እንዲያነቡ በክብር እንጋብዛለን፡፡
አብራችሁን ለመስራት ብትሹ በአድራሻችን እንድታገኙን ይሁን፡፡
+ ስለ ራስ አገዝ ጥምረት ፅንሰ ሀሳብ
በራስ አገዝ ቡድን አሰራር መሰረት ጥምረት 3ኛው ደረጃ ሲሆን ከአባል ሕብረቶች ሁለት ሁለት ተወካዮች በጥንቃቄ ተመርጠው ጥምረቱ ይመሰርታሉ፡፡ በመጀመሪያ ከ 8 እስከ 10 የሚሆኑ ሕብረቶች ጥምረቱን ይመሰርታሉ፤ ከዚያም የአባል ጥምረቶች ቁርጥ እየጨመረ ይሄዳል፡፡ የራስ አገዝ ጥምረት የራሱን ራዕይ፤ ተልኮ እና ግብ ሁሉንም በራስ አገዝ የተደራጁ አባላትን በማሳተፍ በማውጣት፤ ለትግበራው ይንቀሳቀሳል፡፡
በራስ አገዝ አሰራር መሰረት ጥምረት አራት ዋና ዋና የስራ ሚናዎች ይኖሩታል፡፡ እነርሱም፤
1ኛ. ጠንካራ የህዝብ ተቋም መመስረት እና ማስቀጠል
2ኛ. የህብረተሰቡን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ አገልግሎቶችን ማመቻቸት
3ኛ. ለማህበረሰብ ሰላም፤ ደህንነት እና ፍትህ መስራት
4ኛ. በመንግስት ፓሊሲና በህብረተሰቡ አስተሳሰብ ላይ በጎ ተፅዕኖዎችን ማሳደር
+ የጥምረት ለለዉጥ አመሰራረት
ጥምረት ለለዉጥ በአዳማ ከተማ በ9 ህብረቶች እና 74 የራስ አገዝ ቡድኖች የተደራጁ 1173 አባላትን በማካተት ህዳር 18 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡
የቁጥር መረጃዎች ፡- የአባል ቡድኖች ብዛት 74
የሕብረቶች ብዛት 9
ጠቅላላ አባላት ብዛት 1173
የልጆች ብዛት 3518
አጠቃላይ የቡድኖች ቁጠባ 3 ሚሊዩን 209 ሺ 704 ብር
አጠቃላይ አባላት የተሸከረከረ ብድር 11 ሚሊዩን 231 ሺ 049 ብር
አጠቃላይ የአባላት ካፒታል 6 ሚሊዮን 843 ሺ 136 ብር
የጥምረት ለለዉጥ ራዕይ
- በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የበለፀጉ ሴቶችን ማየት፤
ተልዕኮ
- ከማህበረሰቡ እና ከመንግስት ጋር በመሆን የሴቶች ጥቃትን እና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ማስቀረት፡፡
ግብ
እስከ 2015 ዓ.ም ድረስ 1000 የቤት እመቤቶችን በራስ አገዝ ቡድን ማደራጀት፡፡+ በጥምረቱ የሚሰሩ ዋና ዋና ስራዎች
1ኛ. የጥምረቱን ቢሮ ማደራጀት እና ጥምረቱን ቢሮ ማደራጀት እና ጥምረቱን ለተለያዩ አካላት ማስተዋወቅ፤
2ኛ. ከአዳማ ሴቶችና ህፃናት ቢሮ ጋር በመተባበር አመታዊ የራስ አገዝ ቡድን በዓልን ማክበር፤
3ኛ. ከአዳማ ሴቶችና ህፃናት ቢሮ ጋር በመተባበር ፆታዊ ጥቃት በመቃወም ንቅናቄ መድረክ አዘጋጅቷል፤
4ኛ. ለአባል ሕብረቶች የልምድ ልውውጥ እና ራስ በራስ መማማር መድረክ ማዘጋጀት፤
5ኛ. አለም አቀፍ የሴቶች ቀን እና የ16 ቀን ፀረ-ፆታዊ ጥቃት ንቅናቄ ግንዛቤ መድረክ ማዘጋጀት፤
6ኛ. የጥምረቱን ጠቅላላ ጉባዔ አባል ቡድኖችን እና ህብረቶችን በማነቃነቅ መስራት፤
7ኛ. ህብረተሰቡን በማሳተፍ የአካባቢ መንገድ አሰርቷል፤
8ኛ. በግጭት ምክንያት ከአካባቢያቸው ተፈናቅለው በአዳማ ከተማ የተጠለሉ ወገኖችን እገዛ በማሰባሰብ መርዳት፤
9ኛ. በጎዳና ልጆችን እና በችግር ላይ ያሉ ቤተሰቦችን ማገዝ፤
10ኛ. ቡድን እና ህብረቶች እንዲጠነክሩ ሥልጠናዎችን በጊዜው ማመቻቸት፤
11ኛ. ከአጋር ድርጅቶች ጋር ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ ጊዜው የሚጠይቀውን ስራዎችን መስራት፤
12ኛ. የኮሳፕ አመታዊ የጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባዎች ላይ እና ፕሮግራሞች ላይ በቋሚነት መሳተፍ፡፡
+ የጥምረት ለለዉጥ ጥምረት መዋቅር
+ የጥምረቱ አድራሻ
የጥምረት ለለዉጥ ጥምረት
ኦሮሚያ ክልል፤ አዳማ ከተማ
ስልክ ቁጥር 0921074772
ቴሌግራም፡ ጥምረት ለለውጥ
አዳማ፤ ኢትዮጵያ
1. ጥምረት ለለውጥ ሕጋዊ እውቅና አንዳገኘ ያሳወቀበት እና የተባበሩ አጋር አካላትን ያመሰገነበት ፕሮግራም......
2. ጥምረት ለለውጥ በተለያዩ ስልጠናዎች እና ስብሰባዎች ሲሳተፍ.......