Consortium of Self Help Group Approach Promoters (CoSAP) is an umbrella of SHG promoting organizations. Members, who adopt the SHG approach as a key tool for the empowerment of women, utilize this platform as a unifying mechanism for the implementation of the approach. This objective is realized through the provision of capacity building training to member organization and representing them in any policy level discussion that paves the ground for the proliferation of the approach.

+251-115-525251
info@shgconsortiumeth.org
Lideta Sub City, Woreda 10, African Union Area
+251-115-525251

መግቢያ
የራስ አገዝ ጥምረት በራስ አገዝ ቡድን አሰራር መሰረት 3ኛው እና የአሰራሩ መገለጫ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ በስራ ላይ ከሚገኙት ጥምረቶች መካከል ደንበል ጥምረት በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳሚ ቱሉ ጅዶ ኮንቦልቻ ወረዳ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ይህ ጥምረት ድረ ገፅ ስለ ጥምረቱ አመሰራረት እና እንቅስቃሴ የሚያስተዋውቅ ነው፡፡ ስለ ደንበል ጥምረት የበለጠ ለማወቅ ከታች ያሁትን መረጃዎች እንዲያነቡ በክብር እንጋብዛለን፡፡    

+ ስለ ራስ አገዝ ጥምረት ፅንሰ ሀሳብ

በራስ አገዝ ቡድን አሰራር መሰረት ጥምረት 3ኛው ደረጃ ሲሆን ከአባል ሕብረቶች ሁለት ሁለት ተወካዮች በጥንቃቄ ተመርጠው ጥምረቱ ይመሰርታሉ፡፡ በመጀመሪያ ከ 8 እስከ 10 የሚሆኑ ሕብረቶች ጥምረቱን ይመሰርታሉ፤ ከዚያም የአባል ጥምረቶች ቁርጥ እየጨመረ ይሄዳል፡፡ የራስ አገዝ ጥምረት የራሱን ራዕይ፤ ተልኮ እና ግብ ሁሉንም በራስ አገዝ የተደራጁ አባላትን በማሳተፍ በማውጣት፤ ለትግበራው ይንቀሳቀሳል፡፡
በራስ አገዝ አሰራር መሰረት ጥምረት አራት ዋና ዋና የስራ ሚናዎች ይኖሩታል፡፡ እነርሱም፤
1ኛ. ጠንካራ የህዝብ ተቋም መመስረት እና ማስቀጠል
2ኛ. የህብረተሰቡን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ አገልግሎቶችን ማመቻቸት
3ኛ. ለማህበረሰብ ሰላም፤ ደህንነት እና ፍትህ መስራት
4ኛ. በመንግስት ፓሊሲና በህብረተሰቡ አስተሳሰብ ላይ በጎ ተፅዕኖዎችን ማሳደር

+ የደንበል ጥምረት አመሰራረት

ደንበል ጥምረት በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳሚ ቱሉ ጅዶ ኮንቦልቻ ወረዳ በ 12 ህብረቶች እና 106 የራስ አገዝ ቡድኖች የተደራጁ 2292 አባላትን በማካተት በየካቲት 2005 ዓ.ም ተመሰረተ፡፡        
የቁጥር መረጃዎች ፡-     የአባል ቡድኖች ብዛት 106
የሕብረቶች ብዛት 12
ጠቅላላ አባላት ብዛት 2292
አጠቃላይ የቡድኖች ቁጠባ 2 ሚሊዮን መቶ ሺ ብር
አጠቃላይ የቡድኖች ካፒታል 2 ሚሊዮን 630 ሺ ብር
አጠቃላይ ለአባላት የተዘዋወረ ብድር 2 ሚሊዩን 218 ሺ ብር
የደንበል ጥምረት ራዕይ

  • በማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ ፓለቲካዊ የበቁ የሴቶች ህብረት ማየት

ተልዕኮ

  • የማህበረሰቡ እኩልነት መከበሩን ማረጋገጥ፡፡

ግብ

  • ጠንካራ፤ ቆራጥና ጥሩ ተነሳሽነት ያላቸው እና ከማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ድህነት፤ ከባህል ተፅእኖ የተላቀቁ የሴቶች ህበረት መፍጠር፡፡

+ በጥምረቱ የሚሰሩ ዋና ዋና ስራዎች


1ኛ. በስሩ ላሉ የራስ አገዝ ቡድኖችና ህብረቶች የማጠናከር እና ክትትል ድጋፍ መስጠት፤
2ኛ. በህገወጥ የልጆች ዝውውር የተጎዳች ልጅን ጉዳይ ወደ ሚመለከተው የመንግስት አካል በማቅረብ አጥፊዋች እንዲቀጡ አድርጓል፤ ጉዳት የደረሰባትን ልጅ ከቤተሰብ ጋር አቀላቅሏል፤  
3ኛ. አካባቢው ከሚንቀሳቀሱ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመነጋገር ለልጆች የትምህርት መረጃ መሳሪያዎች እገዛ አሰባስቧል፤
4ኛ. ለራስ አገዝ ቡድን አባላት የንብ ማነብ ስልጠና እንዲያገኙ የማመቻቸት ስራ፤
5ኛ. ከቀበሌ ጋር በመተባበር የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ማስተባበር፤
6ኛ. የተለያዩ ስልጠናዎችን ለቡድን እና ህብረት ተወካዮች ማመቻቸት፤
7ኛ. ከአጋር ድርጅቶች ጋር ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ ጊዜው የማይጠየቀውን ስራዎችን ይሰራል፤   
8ኛ. የኮሳፕ አመታዊ የጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባዎች ላይ በቋሚነት ይሳተፋል፡፡

 

+ የደንበል ጥምረት መዋቅር

+ የጥምረቱ አድራሻ

ደንበል ጥምረት
ኦሮሚያ ክልል
ምስራቅ ሸዋ ዞን
አዳሚ ቱሉ ጅዶ ኮንቦልቻ ወረዳ
ስልክ ቁጥር
ኢትዮጵያ